“የተጫዋቾች ደሞዝ ያልከፈልንበት ጊዜ የለም” ወልቂጤ ከተማ

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ደሞዝ ለመክፈል አዳጋች በሆነበት በዚህ ወቅት ወልቂጤ ከተማ ደሞዝ እንዳልከፈለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ተገቢ እንዳልሆነ ክለቡ አሳውቋል።

እንደ ክለቡ ም/ፕሬዝደንት አቶ አበባው ገለፃ ከሆነ ” አንድም ቀን ደሞዝ አለመክፈል አይደለም መደበኛ ክፍያ ከምንከፍልበት ቀን አሳልፈን አናውቅም። የሚያዝያ ወርን በተለያዩ ምክንያቶች ለአምስት ቀን ብቻ ነው ያሳለፍነው። ይህ እየታወቀ ደሞዝ እንዳልከፈልን ተደርጎ የሚቀርቡ ማናቸውም ነገሮች ከእውነት የራቁ ናቸው።” በማለት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኅበር ክለቦች ኮንትራታቸውን አክብረው ስምንት ክለቦች ክፍያ ፈፅመዋል በማለት ማመስገኑ ይታወቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ