ሶከር ታክቲክ | የጨዋታ ዘዴ (system of play)

አሰልጣኝ ደስታ ታደሰ ከተለያዩ ድረ-ገጾች ያገኛቸውን የእግርኳስ ታክቲክ ንድፈ-ሐሳቦችን የተመለከቱ ጥልቅ ትንተናዎች፣ የሥልጠና መመሪያዎች እና መጻህፍትን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ በመተርጎም ሌሎች አሰልጣኞችና አንባቢን ይጠቅም ዘንድ ጥቅም ላይ ለማዋል ይሞክራል፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው ፅሁፍም አንዱ አካል ነው፡፡


– አሰልጣኝ የትኛውንም የጨዋታ ዘዴ ከመምረጡ በፊት እንዴት መጫወት እንደሚፈልግ እና ምን ለማሳካት እንደሚሻ ዕውቀቱ ሊኖረው ይገባል ፡፡
– የአሰልጣኙ ዕይታ እነዚህን ጥያቄዎች በሚመልስበት መንገድ ይመዘናል፡፡

የጨዋታ ዘዴን ስንመርጥ…

 ቡድኑ እንዴት መጫወት እንዳለበት ከመወሰናችና በፊት ብዙ ነገሮች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ፡-

ኳስ በእኛ ቡድን ቁጥጥር ሲሆን እንዴት መጫወት አለብን ?

 በየትኛው ቦታ ለማጥቃት እንጠቀም

 በማጥቃትሂደት ስንት ተጫዋች ይሳተፍ

 በየትኛው መንገድ እናጥቃ ኳስን በመግፋት ፤በማቀበል ፤ወይስ በረጅም በማሻገር

ተቃራኒ ቡድን ኳስ ሲይዝ እንዴት እንጫወት ?

 የትኛውን ቦታ ነው መዝጋት ያለብን

 ተቃራኒ ቡድን ላይ ጫና ማድረግ የምንጀምረው በየትኛው የሜዳ ክፍል ነው

 ከኳስ ጀርባ ስንት ተጫዋች ነው መቅረት ያለበት

 በሜዳ ቁመት እና ስፋት ምን ያህል ተጠቅጥቀናል

ኳስን እንደተነጠቅን እንዴት ምላሽ እንስጥ ?

 እንደተነጠቅን ወዲያው ጫና በማድረግ

 ወደኃላ በማፈግፈግና ክፍተቶችን በመዝጋት

 ወደ ግብ ጠባቂና ወደ ግብ ክልል በመቅረብ

 ምላሽ አሰጣጣችን ኳስን እንደተነጠቅንበት ቦታ ይለያያል

 የጨዋታ ዘዴንባለን ተጫዋቾች እንወስናለን ? ወይስ ለጨዋታ ዘዴያችን የሚሆኑ ተጫዋቾችን እንሰበስባለን ?

 እንደ አሰልጣኝ ሁል ጊዜ ጠንካራ ጎናችንን በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል እና ደካማ ጎናችንን መቀነስ የሚያስችል የጨዋታ ዘዴ መምረጥ ይኖርብናል፡፡

 ተጫዋቾች እንዲጫወቱ በምንፈልግበት የጨዋታ ዘዴ ውጤታማ እንቅስቃሴ ያደርጉ ዘንድ ለጨዋታ ዘዴው የሚሆን የቴክኒክ ጥራት ሊኖራቸው ይገባል፡፡

 ተጫዋቾች የማይችሉትን ነገር እንዲተገብሩ መጠየቅ የተሻለ ተጫዋች እንዲሆኑ አይረዳቸውም ፡፡ ይልቁንስ እኛን ደካማ አሰልጣኝ ያደርገናል፡፡

 ትክክለኛ ወይም ፍፁም የሚባል የአጨዋወት ዘዴ የለም፡፡ ተጫዋቾች በሚጫወቱበት ቦታ ላይ ምን እንደሚጠበቅባቸው ማወቅና ሚናቸውን መለየት የጨዋታ ዘዴው ውጤታማ ይሆን ዘንድ አስፈላጊ ነው ፡፡ ነገር ግን አሰልጣኙ ከእያንዳንዱ ተጫዋች ምን እንደሚፈልግ ግልፅ ማድረግ ይጠበቅበታል ፡፡

 አሰልጣኝ አንዴ የጨዋ ታ ዘዴውን መዝኖ ከመረጠ በኃላ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በሚፈጠር ውጤት ማጣት ስልቱ ላይ እምነት ማጣትና መጠራጠር የለበትም ፡፡በውሳኔያችን ዕምነት ይኑረን፤ አንደናገጥ፤ ፤እናስታውስ- የጨዋታ ዘዴው ግብ አያስገኝም፤ ግብ የሚያስገኘው ተጫዋቹ ነው ፡፡ስለዚህ የመጨረሻው ወሳኝ ነገር የምንይዛቸው ተጫዋቾች የጥራት ደረጃ ነው ፡፡

ሁሉም ቡድኖች በየትኛውም የጨዋታ ዘዴ ሲጫወቱ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ወሳኝ ታክቲካዊ ጉዳዮች

1. ተቃራኒ ቡድንን መጋፈጫ መስመር /line of confrontation/

በሜዳ ላይ ተቃራኒ ቡድንን በመጋፈጥ ጫና ማድረግ የምንጀምርበት ቦታ ነው፡፡ይህ በተቃራኒ ቡድን ላይ ቡድኑ ማሳረፍ የሚፈልገውን የጫና አይነት ያመለክታል፡፡ይህንን መስመር ለመወሰን ብዙ ነገሮችን ማጤን ይኖርብናል

 የአጥቂዎቻችንን ፍጥነት

 የተቃራኒ ቡድን አጥቂዎች ፍጥነት

 የተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች የቴክኒክ ብቃት

 የቡድናችንን ተጫዋቾች የአካል ብቃት ደረጃ

 ከተከላካይ ጀርባ ያለውን ቦታ ለመሸፈን የግብ ጠባቂው ብቃት

 ለማጥቃት ያቀድንበት መንገድ

2. የመጨረሻው ተጫዋች የሚቆምበት መስመር /restraining line/

 የመጨረሻው ተከላካዮች ወደ ጎል ሳይጠጉ እንዲቆሙበት የምትፈልገው ቦታ ፡፡ይህ ቦታ ከፊት ቡድኑ ጫና ማድረግ ከሚጀምርበት ቦታ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው ፡፡

 የመጨረሻዎቹ ተከላካዮች የሚቆሙበት ቦታ ጫና መደረግ ከሚጀምርበት ቦታ ከ 25-30 ሜ. መብለጥ የለበትም።

 ይህ ቡድኑ በጋራ በመጠቅጠቅ ተቃራኒ ቡድን ዘልቀው እንዳይገቡ ያደርጋል ፡፡

ከፍተኛ ወይስ ዝቅተኛ ጫና

 በቡድንህ ውስጥ እና በተቃራኒ ቡድን ውስጥ ያለው የተጫዋች ጥርት የትኛውን ጫና ማድረግ እንዳለብህ የወስናል ፡፡

 ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ ጫና የሚባለው ቡድኑ ተቃራኒ ቡድንን መጋፈጥ ከሚጀምርበት ቦታ በመነሳት ነው፡፡

የትኛውን ዓይነት ጫና ማድረግ እንዳለብን ለመወሰን ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡ ሁኔታዎች

 የአየር ፀባይ ፤የሜዳው ስፋት፤ የሜዳው ሁኔታ

 የጨዋታው ሰዓት

 የጨዋታው ውጤት

 የተጫዋቾች ቁጥር (ቀይ ካርድ )

 በሳምንት ውስጥ ያለው የጨዋታ ብዛት

 የቡድኑ የአእምሮ ሁኔታ


የጽሁፉ ተርጓሚ አሰልጣኝ ደስታ ታደሰ ነው፡፡ አሰልጣኙ ባለፉት አስር ዓመታት በበጎ ፍቃድ ታዳጊዎችን በማሰልጠንና ለበርካታ ክለቦች በማበርከት እውቅና ባተረፈው የአስኮ እግር ኳስ ፕሮጀክት ሲያሰለጥን ቆይቷል ፡፡ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአፍሮ-ፂዮን እግር ኳስ ክለብ ከ17 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡