” አገልግሎት ያላገኘሁበትና አስቀድሞ የከፈልኩት ክፍያ ይመለስልኝ” ሲል ወላይታ ድቻ ለሊግ አክስዮን ምኅበሩ ጥያቄውን በደብዳቤ አቅርቧል።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የ212 ውድድሮች ሙሉ በሙሉ መሠረዛቸውን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ለጨዋታ ታዛቢዎች እና የዳኛ ውሎ አበል 870,000 ብር አስቀድሞ መክፈሉን አስታውሶ ይህ ክፍያ የሰላሳ ሳምንት ያካተተ ቢሆንም ቀሪ ጨዋታ ባለመከናቸውን ምክንያት የ13 ጨዋታ ታሳቢ ተደርጎ ብሩ ተመላሽ ይሁንልን ሲል በደብዳቤ ጠይቀዋል።
በሌላ ዜና የሁለት ወር ደሞዝ አልተከፈለንም ተብሎ በተጫዋቾቹ እየቀረበበት የሚገኘውን ቅሬታ አስመልክቶ ክለቡ እንደገለፀው ከወቅቱ ውስብስብ ችግር አንፃር እንደዘገየ እና በቅርቡ የክለቡ የበላይ ኃላፊዎች አስፈላጊውን ሁኔታ አመቻችተው ክፍያውን ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ተገልጿል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ