ሰበታ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከቡድኑ አጠቃላይ አባላት በተሰበሰበ 453 ሺህ ብር እህል በመግዛት ለከተማ አስተዳደሩ አስረከበ፡፡
በኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት በርካቶች በሀገራችን በስራ እጦት ለችግር እየተዳረጉ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ ረገድ ችግር ያጋጠማቸውን ግለሰቦች፣ አቅመ ደካሞች እና ድርጅቶችን በእግርኳሱ ውስጥ ያሉ በአጠቃላይ የራሳቸውን ድርሻ እስከ አሁኗ ጊዜ ድረስ እየተወጡ ሲገኝ አሁን ደግሞ ተራው የሰበታ ከተማ ሆኗል፡፡ ሰበታ ከተጫዋቾቹ፣ ከአሰልጣኝ ቡድን አባላት፣ ከክለቡ ሰራተኞች እና የተጫዋቾች ካምፕ ሰራተኞች ከደመወዛቸው ላይ 25% (453 ሺህ ብር) በመሰብሰብ ለአቅመ ደካሞች እንዲውል በማሰብ በተዋጣው ገንዘብ ዱቄት በመግዛት ለሰበታ ከተማ አስተዳደር ማስረከቡን የሰበታ ከተማ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ምንዳ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
ሰበታ ከተማ ከወራት በፊት የቡድኑ አጠቃላይ አባላት የደም ልገሳ ስነ-ስርአትን አከናውነው እንደነበረ ይታወሳል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ