የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች የደሞዝ ጥያቄ አሁንም እንደቀጠለ ነው

የሰባት ወር ደሞዝ ተነፍጓቸው ሰሚ ያጡት የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ጉዳያቸውን ይዘው ወደ የተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ቢሮዎችን እየጠየቁ ይገኛሉ።

በተጫዋቾች ደሞዝ ክፍያ ላይ እጅጉን የተቸገረ የሚመስለው የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ጅማ አባ ጅፋር ከእግርኳሳዊ ክንውን ይልቅ ቅሬታ ማስተናገድ የክለቡ የዕለት ተዕለት ስራ ከመሰለ ሰነባብቷል። አንድ ብሎ የተጀመረው የተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ አሁን ላይ ሰባት ወር ደርሷል። ዛሬም እንደ መደበኛ ስራ በተለያዩ ቢሮዎች የቅሬታ ደብዳቤያቸውን ማስገባት ያልቦዘኑት ተጫዋቾቹ ነገን ተስፋ በማድረግ የኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የፃፈላቸውን ደብዳቤ ይዘው ወደ ጅማ አባጅፋር ክለብ አምርተዋል።

በሌላ ዜና በጅማ ትልቅ ሆቴል ውስጥ ለወራት ተቀምጠው የምግብ የአልጋ ወጪ ሳያወጡ የደሞዝ ይከፈለን የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ የቆዩት የውጭ ሀገር ተጫዋቾች በሆቴል አስቀምጦ ክለቡ የሚያወጣውን አላስፈላጊ ወጪ ለመቀነስ ሲባል በስምምነት የሁለት ወር ደሞዝ በመክፈል ቅዳሜ ከጅማ እንደሚወጡ ሰምተናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ