መከላከያ ከ ወላይታ ድቻ ፡ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

መከላከያ 1-2 ወላይታ ድቻ
26’መሃመድ ናስር(ፍ/ቅ/ምት) ፡ 5’52’ አላዛር ፋሲካ
—————–

ተጠናቀቀ!!!!
ወላይታ ድቻ ባለሜዳው መከላከያን በአላዛር ፋሲካ ግቦች 2-1 አሸነፈ፡፡

90′ ባለሜዳዉ መከላከያ ከመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ ቢንቀሳቀሱም ወደ ጎል በመድረስ ወላይታ ድቻዎች የተሻሉ ናቸው፡፡ 4 ተጨማሪ ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

84′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
ዮሴፍ ደንጌቶ ወጥቶ ተከላካዩ ተክሉ ታፈሰ ገብቷል፡፡

83′ ነጂብ ከማእዘን የተሻገረውን ኳስ ሞክሮ ግብ ጠባቂው አሸናፊ አውጥቶበታል፡፡

78′ የተጫዋች ለውጥ መከላከያ
በሀይሉ ግርማ ወጥቶ ቴድሮስ ታፈሰ ገብቷል፡፡

77′ ቴድሮስ በቀለ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

75′ መከላከያዎች ለማጥቃት በወጡበት ወቅት በመልሶ ማጥቃት ድቻዎች በአላዛር አማካኝነት ጥረት ቢያደርጉም ግብ ጠባቂው ይድነቃቸው አድኖታል፡፡

69′ የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
ማራኪ ወርቁ ገብቶ ፍሬው ሠለሞን ወጣ

66′ መከላከያዎች የቅጣት ምት አግኝተው መሀመድ ናስር መትቶ ወደውጪ ወጥቷል፡፡

59′ ሙሉአለም ጥላሁን በግል ጥረቱ ያገኘውን ኳስ ከርቀት ሞክሮ ኢላማውን ስቶ ወደውጪ ወጥቷል፡፡

55′ ከማእዘን የተሻገረዉን ኳስ ዮሴፍ ደንጌቶ ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል፡፡

52′ ጎልልልልል
ፀጋዬ ብርሀኑ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ አላዛር ፋሲካ ድቻን በድጋሚ መሪ አድርጓል፡፡

47′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
መሳይ አጪሶ ገብቶ እንዳለ መለዮ ወጥቷል፡፡

46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ

——-
ተጠናቀቀ!!!
የመጀመርያው አጋማሽ 1-1 ተጠናቀቀ

42′ ወላይታ ድቻዎች በመልሶ ማጥቃት ሲጫወቱ መከላከያዎች ቶሎቶሎ ወደ ግብ እየደረሱ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን የድቻን የተከላካይ መስበር አልቻሉም፡፡

36′ አናጋው ባደግ ለድቻ ሁለተኛ ሊሆን የሚችል ሙከራ ከርቀት ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

26′ ጎልልልል
መሃመድ ናስር የፍፁም ቅጣት ምቱን አስቆጥሮ መከላከያን አቻ አድርጓል፡፡

26′ በድቻ የግብ ክልል በእጅ ኳስ ተነክቶ የፍፁም ቅጣት ምት ለመከላከያ ተሰጠ

24′ ፍሬው ሰለሞን ወደ ግብ የሞከረውን ኳስ አሸናፊ ወደ ውጪ አውጥቶበታል፡፡ መከላከያ ግብ ከተቆጠረበት በኋላ የአቻነት ጎል ፍለጋ ተጭኖ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

16′ ሙሉአለም ጥላሁን ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ አግኝቶ አልተጠቀመበትም፡፡

5′ ጎልልልል
አላዛር ፋሲካ ለወላይታ ድቻ አስቆጠረ

1′ ጨዋታው 09:03 ሲል ተጀመረ

— —- — —

የወላይታ ድቻ አሰላለፍ
ወንድወሰን አሸናፊ
ሙባረክ ሽኩሪ – ቶማስ ስምረቱ – ፈቱዲን ጀማል
አናጋው ባደግ – አማኑኤል ተሾመ – ዮሴፍ ደንጌቶ – በድሉ መርዕድ – ፀጋዬ ብርሃኑ
እንዳለ መለዮ – አላዛር ፋሲካ

– – – – – – –

የመከላከያ አሰላለፍ

ይድነቃቸው ኪዳኔ
ሽመልስ ተገኝ – አዲሱ ተስፋዬ – ቴዎድሮስ ወርቁ – ነጂብ ሳኒ
ሚካኤል ደስታ – በሃይሉ ግርማ – ፍሬው ሰለሞን
ሳሙኤል ታዬ – መሃመድ ናስር – ሙሉአለም ጥላሁን

ያጋሩ