የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ቀጣይ ማረፊያ በቅርቡ ይታወቃል

ላለፉት ሁለት ዓመታት ከምዓም አናብስት ጋር ቆይታ በማድረግ ቡድኑ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ያስቻሉት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የኮንትራታቸው ማብቃትን ተከትሎ ቀጣይ ማረፍያቸው በቅርቡ ይታወቃል።

ከሁለት ዓመታት በፊት ከጅማ አባጅፋር ጋር የሊጉን ዋንጫ ባነሱ ማግስት ክለቡን ለቀው ወደ መቐለ በማምራት የሁለት ዓመታት ውል የተፈራረሙት እኚህ አሰልጣኝ ከክለቡ ጋር ያላቸው ውል በመጠናቀቁ በክለቡ ይቀጥሉ ይሆን ወይስ ቀጣይ ማረፊያቸው የት ይሆናል በሚለው አነጋጋሪ ሆኗል። ሶከር ኢትዮጵያም ከቅርብ ምንጮች ባገኘችው መረጃ አሰልጣኙ ከክለቡ ጋር ውል በሚያራዝሙበት መንገድ ዙርያ ለመነጋገር አንድ ጊዜ ተገናኝተው የተነጋገሩ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ድርድር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በርካታ የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች የአሰልጣኙን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ እንደሆነ በስፋት እየተነገረ ይገኛል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ