ካሣዬ አራጌ በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት ይመለሳል

የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ ወደ በቀጣይ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለስ ያገኘቸው መረጃ ያመለክታል።

አሰልጣኝ ካሣዬ የዛሬ ሦስት ወር ገደማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት መቋረጡን ተከትሎ ለረጅም ዓመታት ወደኖረበና ቤተሰቡ ወደሚገኝበት አሜሪካ ያቀና ሲሆን በቅርብ ቀናት ወደ ሀገር ቤት ተመልሶ የክለቡ ሥራውን ማከናወን እንደሚጀምር ሰምተናል። ከአሰልጣኙ ቀዳሚ ተግባራት መካከል የዝውውር ጉዳዮች እንደሚሆኑ ሲነገር የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር እንደሚያጠናቅቅ ለማወቅ ችለናል።

አሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ ከረጅም ጊዜ የአሜሪካ ቆይታ በኋላ በዓመቱ መጀመርያ በተጫዋችነት እና አሰልጣኝነት ከዚህ ቀደም ያገለገለው ኢትዮጵያ ቡናን ለማሰልጠን በአራት ዓመታት ውል መረከቡ ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ