የሰበታ ከተማው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በክለቡ ለመቆየት ሊሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አሳውቀዋል።
ፋሲል ከነማን በመልቀቅ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የተመለሰው ሰበታ ከተማን በሁለት ዓመት ኮንትራት የተረከቡት አሰልጣኙ ቀሪ ውል ቢኖራቸውም በውላቸው መሰረት ሀመቀጠል በእስካሁኑ ቆይታቸው ደስተኛ ያልሆኑባቸው ጉዳዮችን በመጥቀስ እንዲሻሻሉ ጠይቀዋል። ከነዚህም መካከል በውድድር ዓመቱ ለአሰልጣኙም ሆነ ለተጫዋቾቹ በተገቢ ሁኔታ ክፍያ እየተፈፀመ አለመገኘቱን ገልፀው የእስካሁኑ ክፍያ እንዲፈፀምና ወደፊትም ክፍያዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲከፈሉ ጠይቀዋል። አሰልጣኙ በክለቡ አስተዳደር ላይም ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት ውድድር ቢጀመር ሊከናወኑ የሚገቡ ቅድመ ዝግጀት እና የዝውውር እንቅስቃሴ እስካሁን አለመጀመራቸው ሌላው ያቀረቡት ቅሬታ ነው። አሰልጣኙ እነዚህ ጥያቄዎችን ክለቡ በተገቢው ሁኔታ ምላሽ ካልሰጠ ለቀጣይ ዓመት ለመቀጠል እንደሚቸገሩ ነው ያሳወቁት።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ