የኮሮና ወረርሺኝን ተከትሎ የዝውውር ወቅት መፋለስ የሚያጋጥመው መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ የክረምት የዝውውር መስኮት መቼ ይከፈታል የሚለውን ከፌዴሬሽኑ ጠይቀን በመስከረም ወር እንደሚከፈት አረጋግጠናል።
ያለፉት አራት ወራትን ከእግርኳስ እንቅስቃሴ ውጪ የሆነችው ኢትዮጵያ ወደ ውስጥ ውድድር መቼ እንደምትመለስ ያልታወቀ ቢሆንም በፊፋ የሀገራት የዝውውር ጊዜ የምዝገባ እና የውድድር ካላንደር ላይ ጥቅምት 15 የውድድር ጊዜ መጀመርያ ተብሎ ተቀምጧል። የዝውውር መስኮቱ ደግሞ መስከረም 2 ተጀምሮ ኅዳር 25 እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል። የውድድር ዘመን አጋማሽ መስኮት የካቲት 16 እስከ መጋቢት 16 ድረስ ይቆያል ሲህ ይገልጻል። ይህን መረጃም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አረጋግጦልናል።
ይህን ተከትሎ ከወዲሁ የዝውውር እንቅስቃሴ ላይ የገቡ ክለቦች በይፋ ለማስፈረም የመስከረም መጥባትን ይጠባበቃሉ።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ