የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና የብሔራዊ ቡድን ኮንትራታቸው እንደማይታደስ የተገለፀው አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ዛሬ መነጋገራቸው ታውቋል።
የሁለቱ ግለሰቦች የውይይት ማዕከል የነበረው ከፌዴሬሽኑ ውሳኔ ጋር በተያያዘ የተሰማቸውን ቅሬታ በተለያዩ ሚድያዎች ሲገልፁ የቆዩት አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ቅሬታቸውን ለፕሬዝዳንቱ መግለፃቸው የተሰማ ሲሆን አቶ ኢሳይያስ ጂራ በበኩላቸው ውሉ ያልተራዘመበትን ምክንያት መስረዳታቸው ታውቋል።
ባለፉት ወራት እና በቀጣይ ዓመት ሊከናወኑ መርሐ ግብር የወጣላቸው በርካታ የአፍሪካ እና የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ወደፊት በሚገለፅ ጊዜ መሸጋገራቸው የሚታወቅ ሲሆን በቀጣይ መቼ እንደሚደረጉ አለመታወቁን ተከትሎ ፌዴሬሽኑ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውልን ላለማራዘም መወሰኑን ማሳወቁ ይታወሳል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ