ሀዋሳ ከተማ የሰባት ነባር ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡
አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረትን ከወራት በፊት በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩት ሀዋሳዎች በ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ አሰልጣኙ በርካታ ወጣቶችን ሊጠቀሙ እንደሆነ እየተሰማ ሲሆን በነዚህ ወጣቶች ላይ ልምድ ያላቸውን ጥቂት ተጫዋቾችን ብቻ በዝውውሩ ላይ እንደሚያስፈርም ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡ ክለቡም አዳዲስ ተጫዋቾችን ከማምጣቱ በፊት የነባር ተጫዋቾችን ውል ማራዘም ጀምሯል፡፡
በዚህም መሠረት ከሀዋሳ ታዳጊ ወይንም ተስፋ ቡድን አድገው ክለቡን ያለፉትን ሦስት አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት ተከላካዩ ወንድማገኝ ማዕረግ፣ አጥቂው ቸርነት አውሽ፣ አማካዮቹ ዮሐንስ ሱጌቦ እና ዳዊት ታደሰ እንዲሁም ከደቡብ ፖሊስ ሀዋሳን ተቀላቅሎ የነበረው አጥቂው ሄኖክ አየለ ውላቸው ለተጨማሪ ሁለት እና አንድ ዓመታት ታድሷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ክለቡ ከተስፋ ቡድን ዘንድሮ ላደጉት አጥቂው ሀብታሙ መኮንን እና ግብ ጠባቂው አላዛር ማርቆስ ተጨማሪ ውልን ሰጥቷቸዋል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ