በሀገራችን ተስፋ ከተጣለባቸው ወጣት ዳኞች አንዱ የነበረው ጌድዮን ሄኖክ ከዚህ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ ተወልዶ ያደገውና ከ2005 ጀምሮ በረዳት ዳኝነት ሲያገለግል የቆየው ጌድዮን ፈጣን መሻሻል በማሳየት ወደፊት ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊሆኑ ከሚችሉ ተስፈኛ ወጣቶች አንዱ የነበረ ሲሆን በ2009 ከ17 ዓመት በታች ኮከብ ረዳት ዳኛ እንዲሁም በ2011 የአንደኛ ሊግ ኮከብ ረዳት ዳኛ (ፎቶ) ሆኖ መሸለም ችሎ ነበር።
ይህ ወጣት ዳኛ ትናንት ማምሻውን በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ የተገለፀ ሲሆን በነገው ዕለት ካራ መድኃኒያለም ቤተ ክርስቲያን የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ይፈፀማል።
ሶከር ኢትዮጵያ በጌድዮን ሄኖክ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለሙያ አጋሮቹ መፅናናትን ትመኛለች።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ