ሴናፍ ዋቁማ ወደ አውሮፓ…?

የ2011 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋቿ ሴናፍ ዋቁማ በአውሮፓ ከሚገኝ ክለብ ጥያቄ እንደቀረበላት መረጃዎች እየወጡ ነው።

ያለፉትን ተከታታይ አራት ዓመታት በሴቶች እግርኳስ ብቅ ብላ ስኬታማ የሆነ እግርኳስ ህይወቷን በመምራት ጎልታ መውጣት የቻለቸው እና የጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ ፍሬ የሆነችው ሴናፍ ዋቁማ ወደ አውሮፓ ወጥታ የምትጫወትበት እድል እየተመቻቸላት እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። ስሙ ለጊዜው ያልተገለፀውና በቀጣይ የውድድር ዘመን በአውሮፓ ሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ በሆነ ክለብ ጥያቄ እንደመጣ እና በቅርብ ጊዚያት ሴናፍ ከፈላጊ ክለቧ ጋር አስፈላጊው ውይይት እና የሜዳ ላይ እንቅስቃሴዋን የሚያሳዩ ቪዲዮችን በመላክ ጉዳዩን መከታተል እንደምትጀምር ለማወቅ ችለናል።

ከዚህ ቀደም ሴናፍ ዋቁማ እና ሰናይት ቦጋለ ለሙከራ ወደ ስዊድን አምርተው ከቆይታ በኃላ መመለሳቸው ሲታወስ በሎዛ አበራ የተገመረው ኢትዮጵያውያን ሴት ተጫዋቾች ወደ በአውሮፓ ሊግ ወጥተው የመጫወት አዲስ ምዕራፍ በቀጣይ በሴናፍ ዋቁማ ሊቀጥል እንደሚችል ተገምቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ