ወልቂጤ አዲስ ተጫዋች ለማስፈረም ሲስማማ የአጥቂውን ውል አድሷል

ወልቂጤ ከተማ ሁለተኛውን አዲስ ተጫዋች ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ሲስማማ የአንድ የነባር ተጫዋች ውል አራዝሟል።

በዛሬው እለት በሁለት ዓመት ውል ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል የተስማማው የፊት መስመር ተጫዋቹ ምንይሉ ወንድሙ ነው። በመከላከያ ዋናው ቡድን ከ2007 ጀምሮ ሲጫወት የቆየው ምንይሉ ባለፉት ዓመታት በሊጉ ከታዩ ጥሩ የአጥቂ መስመር ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን በተሰረዘው ውድድር ዓመት የጎል አስቆጣሪ ችግር ለነበረበት ወልቂጤ እፎይታ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

በክለቡ ለመቀጠል ውሉን ያራዘመው ተጫዋች አሕመድ ሁሴን ነው። ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደረገው ፈጣኑ አሕመድ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን ለሁለት ዓመት በቡድኑ ለመቆየት ተስማምቷል። አሕመድ ከአዲስ ፈራሚው ምንይሉ ጋር የተሻለ ጥምረት ይፈጥራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ