መናፍ ዐወል ባህርዳር ከተማን ተቀላቀለ

ከአዳማ ከተማ ወጣት ቡድን ተገኝቶ ክለቡን ሲያገለግል የነበረው መናፍ ዐወል ለባህርዳር ከተማ ፊርማውን ለማኖር ተስማማ፡፡

ከሰሞኑ የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ተጠምደው የሰነበቱት ባህርዳር ከተማዎች የመጀመሪያውን አዲስ ተጫዋች ሲቀላቅሉ የመስመር እና የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ መናፍ ዐወል ለመፈረም የተስማማ ተጫዋች ሆኗል። ከአዳማ ከተማ የታዳጊ ቡድን ካደገ በኃላ በክለቡ ከ2009 ጀምሮ ለአራት ዓመታት ሲያገለግል የቆየው ይህ ወጣት ተከላካይ በተሰረዘው የዘንድሮ የውድረር ዓመት ድንቅ ጊዜ ማሳለፍ ችሎ ነበር።

በጣና ሞገዶቹ ቤት በሁለት ዓመት የውል ዕድሜ ለመቆየት የተስማማው መናፍ በርካታ ጎሎች ሲያስተናግድ የቆየው የባህር ዳር የተከላካይ መስመር ላይ ጥንካሬ እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ