ባህር ዳር ከተማ የተጨማሪ ተጫዋች ውል አድሷል

ዛሬ ረፋድ የአንድ ተጫዋች ዝውውር ያጠናቀቁት የጣናው ሞገዶቹ 7ኛ ነባር ተጫዋቻቸውን ውል ከደቂቃዎች በፊት አድሰዋል።

ትላንት ማምሻውን አዲስ አበባ በመምጣት የነባር ተጫዋቾችን ውል በማደስ ላይ የሚገኙት የባህር ዳር ከተማ አመራሮች ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ የሁለገቡን ተጫዋች ሚኪያስ ግርማን ውል አድሰዋል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ ቡድን የተገኘው ሚኪያስ ግርማ በ2009 በውሰት ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ አምርቶ ከግማሽ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ባህር ዳር ከተማ በማቅናት ለ18 ወራት ቆይታን አድርጎ ለሙከራ ወደ ታይላን ማምራቱ ይታወሳል። ሚኪያስ የታይላንዱን ሙከራ አገባዶ ከመጣ በኋላ ወደ ድሬዳዋ ከተማ በማምራት ግልጋሎት ሰጥቷል። ከዛም በኋላ ዳግም ወደ ጣና ሞገዶቹ ቤት ጉዞውን በማድረግ መልካም የሚባል ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል። በተከላካይ፣ አማካይ እንዲሁም አጥቂ ቦታ ላይ መጫወት የሚችለው ይህ ተጫዋች በዛሬው ዕለት ውሉን ለ2 ዓመታት አድሷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ