የጣና ሞገዶቹ የተጫዋቾቻቸውን ውል ማደሳቸውን ቀጥለዋል

የነባር ተጫዋቾችን ውል ማደስ ላይ ተጠምደው የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊትም የሁለት ተጫዋቾን ውል አራዝመዋል።

ከደቂቃዎች በፊት ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ከጣናው ሞገዶቹ ጋር ለመቆየት ፊርማቸውን ያኖሩት ሳላምላክ ተገኝ እና ሰለሞን ወዴሳ ናቸው። ከኢትዮጵያ ቡና ባህር ዳርን መጀመሪያ በውሰት ቀጥሎም በቋሚነት ተቀላቅሎ ቡድኑን ሲያገለግል የነበረው ሳላምላክ በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ይሁኝታ መሰረት ከቡድኑ ጋር ለመቆየት የተስማማ የመጀመሪያው ተጫዋች ነው። በመስመር ተከላካይ፣ አማካይ እና አጥቂ ቦታ ላይ ተሰልፎ መጫወት የሚችለው ይህ ተጫዋች ለአሰልጣኙ ጥሩ አማራጭ መስጠቱን ይቀጥላል ተብሎ ይታሰባል።

ሁለተኛው ውሉን ያራዘመው ተጫዋች ሰለሞን ወዴሳ ነው። በሃዋሳ ከተማ አድጎ ወደ ኢትዮጵያ መድን ያቀናው ይህ ወጣት የመሃል ተከላካይ በዘንድሮ የውድድር ዘመን ከጣና ሞገዶቹ ጋር መልካም ጊዜን ማሳለሁ ይታወቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ