ወልቂጤ ከተማ ከአንጋፋው ተጫዋች እና ምክትል አሰልጣኙ ጋር ተለያይቷል

አዳነ ግርማ እና ወልቂጤ ከተማ መለያየታቸውን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።

በተሰረዘው ውድድር ዓመት ሀዋሳ ከተማን ለቆ ወደ ሌላኛው ደቡብ ቡድን የተቀላቀለው አንጋፋው ተጫዋች በተለይ በመጀመርያዎቹ ሳምንታት በተጫዋችነት ክለቡን ሲያገለግል የነበረ ሲሆን በተጨማሪነትም ምክትል አሰልጣኝነትም ሲሰራ እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ዓመት ከተጫዋችነት እንደሚገለል የተነገረለት የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ከክለቡ ጋር በስምምነት እንደተለያየ የክለቡ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መላኩ ለሶከር ኢትዮጽያ ገልፀዋል።

አዳነ ግርማ በቅርቡ ባየርን ሙኒክ ያዘጋጀው የጀማሪ አሰልጣኞች ስልጠና ላይ መካፈሉ ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ