የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማካይ ጉዳት አስተናገደ

የአብስራ ተስፋዬ ጉዳት ማስተናገዱን ክለቡ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።

ተጫዋቹ በልምምድ ላይ ሳለ በክርን አጥንቶቹ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት የተገለፀ ሲሆን ወደ ሆስፒታል አምርቶ ቀዶ ጥገና ተደርጎለታል። ከጉዳቱ ለማገገም እስከ ስድስት ወራት ሊወስድበት እንደሚችልም ተገልጿል።

የአብስራ ደደቢትን ለቆ በ2011 ክረምት ቅዱስ ጊዮርጊስን መቀላቀሉ የሚታወስ ነው።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ