የአዳማ ከተማ አመራሮች አዳዲስ ውሳኔዎችን አሳለፉ

በዘንድሮ ዓመት በተለያዩ ምክንያቶች የተቀዛቀዘ የውድድር ጊዜ ያሳለፈው አዳማ ከተማ ለቀጣይ ዓመት ራሱን ለማዘጋጀት ወደ እንቅስቃሴ ሊገባ ነው።

አዲስ የተሾሙት የክለቡ ፕሬዝደንት አቶ ገመቹ በተገኙበት የክለቡ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በትናንትናው ዕለት በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። ክለቡ አዲስ አሰልጣኝ ለጊዜው እንደማይቀጥር እና በምክትል አሰልጣኞቹ አማካኝነት ቡድኑ እንዲመራ ወስነዋል። ከዚህ በተጓዳኝ ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን በክለቡ ለማቆየት ውል የማደስ ስራ እንዲሰራ፣ ወደ ክለቡ እንዲመጡ የታሰቡ አዳዲስ ተጫዋቾችም ካሉ ፌዴሬሽኑ ባስቀመጠው የዝውውር መመርያ ደንብ መሠረት እንዲፈርሙ፣ እንዲሁም ከወጣት ቡድን የሚያድጉ ብቁ ተጫዋቾች ካሉ ተገቢው ምልመላ ተደርጎ ወደ ዋና ቡድን እንዲያድጉ አቅጣጫ በመስጠት ተጠናቋል።

በዛሬው ዕለት የቡድኑ የአሰልጣኝ አባላት በሙሉ በተገኙበት ከቡድኑ አመራሮች ጋር ውይይት በማድረግ ከነገ ጀምሮ ኮንትራታቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን በቡድኑ ለማቆየት ንግግር እንደሚጀምሩ የሰማን ሲሆን ክፍተት አሉባቸው በተባሉ ቦታዎች አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈራም እንደሚንቀሳቀሱ ለማወቅ ችለናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ