የአንጋፋዋ የቅዱስ ጊዮርጊስ የልብ ደጋፊ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ ተፈፀመ

የረጅም ዓመት የቅዱስ ጊዮርጊስ አባል፣ ቤተሰብና የቅርብ አገልጋይ የነበረችው ካሰች መስቀሌ የቀብር ሥነ ስርዓት በርካታ የስፖርት ቤተሰብ በተገኘበት ተፈፅሟል።

ከልጅነት እስከ እውቀት ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን በደገፍ በማስተባበር ለበርካታ ደጋፊዎች ምሳሌ በመሆን የምትታወቀው ወ/ሮ ካሰች መስቀሌ የማረፋቸው ዜና በትናትናው ዕለት መሰማቱ ይታወቃል።

በዛሬው ዕለት አስኮ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በተገኙበት ግባተ መሬታቸው በክብር ተፈፅሟል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ