ሀዲያ ሆሳዕና አራተኛ ተጫዋቹን ለማስፈረም ተስማምቷል

በዛሬው ዕለት የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቆ የነበረው ሀዲያ ሆሳዕና ኃይሌ እሸቱን አራተኛ ፈራሚ በማድረግ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ፣ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ አጥቂ ባለፈው ክረምት ወላይታ ድቻን ለቆ በአዳማ ከተማ ቆይታ ያደረገ ሲሆን እንደ አዲስ ህንፃ፣ በረከት ደስታ እና ቴዎድሮስ በቀለ ሁሉ የቀድሞ አሰልጣኙ ፈለግን በመከተል በአንድ ዓመት ውል ወደ ነብሮቹ አምርቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም 👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ 👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ