በ2011 የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለውይይት አቅርቦ በውሳኔ የተጠናቀቀው የተጫዋቾች ደሞዝ ጣርያ መጠን ተገቢ አይደለም በሚል የተጫዋቾች ማኅበር ተቃወመ።
በ2011 ቢሸፍቱ ከተማ በሚገኘው ሊዛቅ ሪዞርት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በተጫዋቾች ደሞዝ አስመልክቶ የሚመለከታቸውን ባለ ድርሻ አካላት በሙሉ ባይባልም የ2012 የውድድር ዘመን ክለቦች ለተጫዋቾች የሚከፍሉትን የደሞዝ ጣርያ ከ50ሺህ እንዳይበልጥ መወሰኑ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ በወቅቱ የተለያዩ ጥያቄዎች በውሳኔው ዙርያ ተነስተው ሲያከራክሩ መቆየታቸው አይዘነጋም። በዛሬው ዕለትም የተጫዋቾች ማኅበር ከዚህ ቀደም የተወሰነው ውሳኔ የተጫዋቹን መብት ያላከበረ፣ የጉዳዩ ባለቤት ያልተገኘበት ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ በመሆኑ እና የአሰሪና የሰራተኛን የድርድር ደንብ ህግ የጣሰ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ያለውን አቋም በሁለት ገፅ ደብደቤ አሳውቋል።
በዋናነት የደብዳቤው ይዘት ያተኮረው በቢሸፍቱ የተካሄደው ስብሰባ ለውይይት እንጂ ለውሳኔ ያልተጠራ ባለመሆኑ፣ የተጫዋቹን የመደራደር መብት የነፈገ በመሆኑ፣ የዓለም ዓቀፍ የአሠሪና ሠራተኛን ህግ እና ስምምነቶችን የጣሰ በተጨማሪም የተጫዋቾች የደሞዝ ጣርያ የሚለው አካሄድ መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ግብር እያሳጣው በመሆኑ ከ2013 ጀምሮ ዓለም አቀፍ አሰራር የተከተለ የእግርኳሱ የበላይ አካል ፊፋ በወጣው የተጫዋቾች አቀጣጠር መመርያ ባሟላ መልኩ እንዲሆን ማኅበሩ አሳስቧል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ