ሀዲያ ሆሳዕና የጋናዊውን አጥቂ ውል አራዝሟል

ጋናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ቢስማርክ አፒያ በነብሮቹ ቤት ውሉን ለማደስ ተስማምቷል።

በ2010 ክረምት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጅማ አባ ጅፋርን የተቀላቀለውና መስመር አጥቂነት እንዲሁም በመሐል አጥቂ ስፍራ ላይ ተሰልፎ መጫወት የሚችለው ጋናዊው ቢስማርክ አፒያ ጅማን ለቆ በስሑል ሽረ በ2011 የውድድር ዘመን በመጫወት ካሳለፈ በኃላ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ሀድያ ሆሳዕናን ተቀላቅሎ መጫወት ችሏል፡፡ ምንም እንኳን ክለቡ ያልተሳካ ዓመትን ቢያሳልፍም ይህ ተጫዋች በግል መልካም እንቅስቃሴን ማድረግ በመቻሉ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለመቆየት ፊርማውን ለማኖር ተስማምቷል፡፡

እስከ አሁን አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመው ክለቡ ከቢስማርክ ውጪ ያሉ ነባር ተጫዋቾችን ውል ለማደስ በድርድር ሒደት ላይ እንደሚገኙ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ ነግረውናል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ