ሰበታ ከተማ የመጀመርያ ተጫዋቹን አስፈረመ

ሰበታ ከተማ በዝውውር ገበያው በመግባት የመጀመሪያ ተጫዋቹን አማካዩ ዳንኤል ኃይሉ አድርጓል፡፡

ከሰሞኑ ለተጫዋቾቻቸው የተነሳባቸውን የደመወዝ ክፍያ በማጠናቀቅ እፎይታን ያገኙት ሰበታ ከተማዎች የአማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ ዳንኤል ኃይሉን የግላቸው አድርገዋል። በባህር ዳር ከተማ ከከፍተኛ ሊጉ ጀምሮ መልካም እንቅስቃሴን ሲያደርግ የነበረው ዳንኤል በአንድ ዓመት ውል ነው ወደ ሰበታ ለማምራት የተስማማው፡፡

ሰበታ ከተማ በቀጣይ ቀናትም አዳዲስ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርሙ ሲጠበቅ ከኃይለሚካኤል አደፍርስ ቀጥሎ ተጨማሪ ነባር ተጫዋቾችን ውል ያራዝማልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ