የአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ቡድን የግርማ በቀለ እና አበባየው ዮሐንስን ውል አራዝሟል፡፡
የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ፣ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ተጫዋች ግርማ በቀለ ውሉን ለተጨማሪ ዓመት በሲዳማ አራዝሟል፡፡ 2011 ኤሌክትሪክን ከለቀቀ በኃላ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና የቆየው ይሄ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ከተከላካይነቱ ባለፈ ወደ አማካይ ተከላካይነት መለስ እያለ ክለቡን በወጥነት ያገለገለ ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከቀናት በፊት የቃል ስምምነት ካደረገ በኃላ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በክለቡ ለመቆየት በመፈረም ተስማምቷል፡፡
ሌላኛው ውሉን ለሁለት ዓመት ያራዘመው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አበባየው ዮሐንስ ነው፡፡ የቀድሞው የስልጤ ወራቤ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ደቡብ ፖሊስ ተጫዋች ሲዳማ ቡናን ዐምና ከተቀላቀለ ጊዜ አንስቶ ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን እያሻሻለ በመምጣቱ ውሉም ዘንድሮ በክለቡ በመጠናቀቁ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ቢነሳም በስተመጨረሻ ውሉን ለሁለት ዓመት አድሷል።
ዛሬ የግብ ጠባቂው መሳይ አያኖን ውል ረፋድ ላይ ያራዘመው ክለቡ ከዚህ ቀደም የብርሀኑ አሻም፣ ሚሊዮን ሰለሞን፣ ሰንደይ ሙቱክ፣ ግሩም አሰፋ፣ ፍቅሩ ወዴሳ እና ይገዙ ቦጋለን ውል ማደሱ ይታወሳል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ