አዳማ ከተማዎች ሁለት የመስመር ተከላካዮች ለማስፈረም በመስማማት ወደ ዝውውሩ ገብተዋል።
በዝውውር መስኮቱ በርካታ ተጫዋቾች ከማጣት ውጭ የተጫዋቾች ውል ሳያራዝሙ እና አዳዲስ ተጫዋቾች ሳያዘዋውሩ የቆዩት አዳማ ከተማዎች አንሷር መሐመድ-ሰዒድ እና አንዋር መሐመድ-ሰዒድ የተባሉ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በማስማማት ነው ወደ ገበያው የገቡት።
የእግርኳስ ሕይወቱን በኮምቦልቻ የጀመረው አንሷር የግራ ተከላካይ ሲሆን ከዚ በፊትም በወልድያ ከተማ ቆይታ አድርጓል። በዚህ ዓመትም በደሴ ከተማ ሲጫወት መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል። ሁለተኛው የአዳማ ከተማ ፈራሚ አንዋር ደግሞ ባለፈው ዓመት ደሴ ከተማን በአምበልነት የመራ ሲሆን ክለቡን በቀኝ መስመር ተከላካይነት ሲያገለግል ቆይቷል። እግርኳስን በደሴ የጀመረው አንዋር ከዚህ በፊት በአማራ ፖሊስ መጫወትም ችሏል።
በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር መስኮቱ የገቡት አዳማዎች በቀጣይ ዓመት በወጣቶች የተገነባ ቡድን ለመስራት በዝግጅት እንደሚገኙ ለማወቅ ሲቻል የክለቡ አመራሮችም የቀድሞ አሰልጣኛቸው ነባር የክለቡ ተጫዋቾችን በማስኮብለሉ ደስተኛ እንዳልሆኑ ሰምተናል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ