በወላይታ የተፈጠረ ግርግርው የአረካ ከተማው አክሊሉ ዋናን ህይወት ቀጥፏል፡፡
በወላይታ ድቻ ከ17 ዓመት በታች ቡድን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ከተጫወተ በኋላ በ2011 ወደ አረካ ከተማ አምርቶ እየተጫወተ ይገኝ የነበረው የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ በአንደኛ ሊጉ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበር ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡ ይሁንና በሀያዎቹ መግቢያ ዕድሜው እንደሆነ የሚነገርለት ወጣቱ ተጫዋች በትውልድ ከተማው ቦዲቲ በተነሳው ግርግር በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ሶከር ኢትዮጵያ በዚህ ወጣት እና ተስፈኛ ተጫዋች ህይወት ማለፍ ምክንያት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ እና ለክለቡ አባላት መፅናናትን ይመኛል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ