ሀዋሳ ከተማ የወሳኙን አጥቂ ውል አራዝሟል

ብሩክ በየነ በሀዋሳ ከተማ ውሉን ለማራዘም ከስምምነት ደርሷል።

ከሀዋሳ ዓመታዊው የቄራ ሻምፒዮና ከተገኘ በኃላ በ2009 በቀጥታ ለወልቂጤ ከተማ ለከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ በነበረበት ወቅቶ በመፈረም ሁለት ድንቅ የውድድር አመታትን በክለቡ በመጫወት አሳልፏል የአጥቂ ስፍራ እና የመስመር አጥቂው ብሩክ በየነ በ2011 መስከረም ወር ላይ ለሀዋሳ ከተማ ፈርሞ ሁለት ድንቅ ዓመታትንም በክለቡ ቆይታው ማሳየት ችሏል፡፡ በተለይ ዘንድሮ በተሰረዘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ ሲፎካካር የነበረ ሲሆን ውሉም መጠናቀቁን ተከትሎ በተለያዩ የፕሪምየር ክለቦች ሲፈለግ ቢሰነብትም በመጨረሻም በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረቱ ሀዋሳ ለሁለት ተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል፡፡

በዝውውር ገበያው ዘግየት ያለው ሀዋሳ ከነማ ከሰሞኑ እንቅስቃሴ እንደሚጀምር የሚጠበቅ ሲሆን እስከ አሁንም ክለቡ ውላቸውን ያራዘመላቸውን ተጫዋቾች ቁጥር ስምንት አድርሷል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ