ወልቂጤ ከተማ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ

ጀማል ጣሰው ወደ ወልቂጤ ከተማ ለማምራት ቅድመ ስምምነት ፈፀመ።

በእግር ኳስ ሕይወቱ ለሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ደደቢት ፣ ጅማ አባ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ የተጫወተው ይህ ግብ ጠባቂ ባለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በፋሲል ከነማ ያሳለፈ ሲሆን ወደ ወልቂጤ ለማምራት መስማማቱን ተከትሎ ወደ ፋሲል ያመራው ይድነቃቸው ኪዳኔን ቦታ ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል።

በዝውውር መስኮቱ የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾች ለማስፈረም በመስማማት ንቁ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚገኙት ወልቂጤዎች እስካሁን ሁለት ግብ ጠባቂዎችን ጨምሮ ስድስት ተጫዋቾች ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ