ሀዲያ ሆሳዕና የተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል

ሀዲያ ሆሳዕና የሄኖክ አርፊጮ፣ ፀጋሰው ዴሌሞ እና መስቀሉ ለቴቦን ውል አራዝሟል፡፡

ከዚህ ቀደም በክለቡ ቆይታ የነበረው እና 2011 ላይ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ ከተጫወተ በኃላ በድጋሚ ወደ ቀደም ክለቡ ተመልሶ ጥሩ ግልጋሎትን ሰጥቷል።

ሁለተኛው ውሉን ያራዘመው ተጫዋች ተከላካዩ ፀጋሰው ዴሌሞ ረዘም ያለ ጊዜን በክለቡ ያሳለፈ ሲሆን ዘንድሮ ባሳየው መልካም እንቅስቃሴ መነሻነት አሁንም ዳግም በክለቡ ቆይታን ለማድረግ ውሉን አድሷል፡፡

የመስመር ተከላካዩ መስቀሉ ለቴቦ ውሉን ያራዘመ ሌላኛው ተጫዋች ነው፡፡ አርባምንጭ ከተማን ለቆ ወደ ቀደም ክለቡ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ዳግም የተመለሰው ተጫዋቹ ተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለማሳለፍ ቅድመ ስምምነት ፈርሟል፡፡

ስለ ውል መራዘሙ ተጫዋቾቹም ሆነ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ