ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፡ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
—————–
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው ካለግብ ተፈፀመ

90+2 ምንተስኖት ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ፌቮ ጨርፏት ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥታለች፡፡

90′ ጨዋታው ካለግብ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡ ተመልካቹም ስታድየሙን ለቆ እየወጣ ነው፡፡

86′ ከቀኝ መስመር የተሻገረውን የቅጣት ምት ፌቮ ወጥቶ አርቆታል፡፡ ፌቮ በሜዳ ላይ በሚያሳየው ድርጊት ተመልካቹን እያዝናና ይገኛል፡፡

81′ የተጫዋች ቅያሪ – ጊዮርጊስ
ዘካርያስ ቱጂ በበኃይሉ አሰፋ ተቀይሮ ገብቷል፡፡

78′ የተጫዋች ቅያሪ – ባንክ
ጌቱ ረፌራ ፊሊፕ ዳውዚን ቀይሮ ገብቷል፡፡

72′ የተጫዋች ቅያሪ – ጊዮርጊስ
አቡበከር ሳኒ በራምኬል ሎክ ተቀይሮ ገብቷል፡፡

71′ የተጫዋች ቅያሪ – ባንክ
ሲሳይ ቶሊ ወጥቶ አምሃ በለጠ ገብቷል፡፡

70′ በኃይሉ አሰፋ የመታው ቅጣት ምት በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

69′ ኤፍሬም በጥሩ የመልሶ ማጥቃት ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ በኦዶንካራ ተይዞበታል፡፡

67′ ምንተስኖት ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

65′ ኤፍሬም አሻሞ ከቀኝ መስመር
የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ወደ ግብ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

64′ የንግድ ባንክ የመከላከል አደረጃጀት ጥሩ ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በረጅሙ ወደ አጥቂዎች ኳስ በመጣል የግብ እድል ለመፍጠር እየጣሩ ይገኛሉ፡፡

55′ ከማዕዘን ምተት የተሻገረውን ኳስ ራምኬል ሎክ ሞክሮ ዳንኤል ከግቡ መስመር አውጥቶታል፡፡

54′ ሁለቱም ቡድኖች በመሃል ሜዳ የተገደበ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡ ለአዳነ በረጅሙ የተላከውን ኳስ
ፌቮ ቀድሞ ይዞታል፡፡
*ምንያህል ተሾመ በእረፍት ሰአት አሉላን ቀይሮ ገብቷል፡፡

46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ፡፡ ጊዮርጊስ ከግራ ወደ ቀኝ ፣ ባንክ በተቃራኒው ያጠቃሉ፡፡

ሁለቱም ቡድኖች ከመልበሻ ክፍል ወጥተዋል፡፡

———-

ተጠናቀቀ!!!!
የጨዋታው የመጀመርያ አጋማሽ ካለግብ
ተጠናቋል፡፡

42′ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዝግታ ወደ ባንክ የግብ ክልል ለመድረስ ሲጥር ንግድ ባንኮች በመስመር አማካዮቹ ሲሳይ እና ኤፍሬም አማካኝነት ጫና ለመፍጠር በመጣር ላይ ናቸው፡፡

40′ አሉላ ግርማ በሰራው ጥፋት ከአርቢቴር በአምላክ ተሰማ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመዞበታል፡፡

38′ ዳንኤል አድሃኖም ከመስመር አክርሮ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

37′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል፡፡

26′ እስካሁን ባለዉ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጊዮርጊሶች ወደ ጎል በመድረስ ረገድ የተሻሉ ናቸው፡፡

20′ አዳነ ግርማ ከምንተስኖት አዳነ ያገኘዉን ኳስ በግብ ጠባቂው አናት ላይ ቢልከውም ዳንኤል አድሀኖም ደርሶ አዉጥቶታል፡፡

12′ በሀይሉ አሰፋ የሞከረውን የቅጣት ምት ግብ ጠባቂዉ ፌቮ አድኖበታል፡፡

7′ አሉላ ግርማ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ አዳነ ግርማ ወደ ግብ ሞክሮ ወደ ወጭ ወጥቶበታል፡፡

2′ አዳነ ግርማ በግንባሩ የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው ፊቮ ሳይቸገር መልሶታል፡፡

1′ ጨዋታው ተጀመረ

የሁለቱም ቡድን ተጨዋቾች ወደ ሜዳ ገብተዉ በማማሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

———

የንግድ ባንክ አሰላለፍ

ፊቮ ኢማኑኤል
አንተነህ ገብረክርስቶስ – ቢኒያም ሲራጅ – አቤል አበበ – ዳንኤል አድሃኖም
ጋብሬል አህመድ – ሰለሞን ገብረመድህን – ኤፍሬም አሻሞ – ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን – ሲሳይ ቶሊ
ፊሊፕ ዳውዚ

—-

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
ሮበርት ኦዶንካራ
መሀሪ መና – አስቻለው ታመነ – አይዛክ ኢሴንዴ – አንዳርጋቸው ይላቅ
አሉላ ግርማ – ምንተስኖት አዳነ – ናትናኤል ዘለቀ
በሀይሉ አሠፋ – አዳነ ግርማ – ራምኬል ሎክ

ያጋሩ