ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ተራዘሙ

የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዓለም ዋንጫ የማጣሪያ መርሀ ግብሮች ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝመዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞችን ውል አላራዝምም በማለቱ የተነሳ በያዝነው ወር መጨረሻ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታ መደረጉም አጠራጣሪ እንዳደረገው በዘገባችን መግለፃችን ይታወሳል፡፡ በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የመጀመሪያውን የማጣሪያ መርሀ ግብር በድል ተወጥቶ ከዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለተኛ ማጣሪያውን በቅርቡ እንደሚያደርግ ቢጠበቅም ካፍ በነሀሴ ወር መጨረሻ ሊካሄዱ የነበሩ የከንደኛ ዙር ጨዋታዎችን ላልታወቀ ጊዜ በማራዘሙ እንቅስቃሴ ውስጥ ከመግባት ተቆጥቦ የነበረው ብሔራዊ ቡድናችን እፎይታን አግኝቷል፡፡

ካፍ ውድድሩን ስለማራዘሙ ከመግለፁ ውጪ ቀን ያልቆረጠ ሲሆን ወደፊት ሥራ አስፈፃሚው ከተነጋገረ በኃላ የሚደረጉበት ጊዜ ይገለፃል ሲል ካፍ በድረገጹ ጠቁሟል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ