ስንታየው ታምራት እና በረከት ወልደዮሐንስ ውላቸውን አድሰዋል፡፡
የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ በረከት ወልደዮሐንስ አርባምንጭ ከተማን ለቆ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ጅማሮ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሀዲያ ሆሳዕና ተመልሶ ያሳለፈ ሲሆን የአንድ ዓመት ውሉን በማጠናቀቁ ለተጨማሪ ዓመት ግልጋሎት ለመስጠት ተስማምቷል፡፡
ከደደቢት ተስፋ ቡድን የተገኘው ስንታየው ታምራት ሌላው ውሉን ለተጨማሪ ዓመት በነብሮቹ ቤት ለመቆየት የተስማማ ነው፡፡ ይህ ግብ ጠባቂ በተሰረዘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለክለቡ ግልጋሎት መስጠት ያልቻለ ቢሆንም ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በክለቡ ለመቆየት ተስማምቷል፡፡
ሀዲያ ሆሳዕና እስከ አሁን በድምሩ የአምስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያራዝሙ አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ለማስፈረም መስማማታቸውም ይታወሳል፡፡
ተጫዋቾቹ ውላቸውን ለማራዘም ቅድመ ስምምነት መፈፀማቸውን ሁለቱም ተጫዋች ሆኑ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ አረጋግጠውልናል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ