አዳነ በላይነህ በወልቂጤ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል

ወልቂጤ ከተማ የመስመር ተከላካዩ አዳነ በላይነህን ለተጨማሪ ዓመታት ለማቆየት ከስምምነት ደርሷል።

በተቋረጠው ውድድር ዓመት የመጀመርያ የፕሪምየር ሊግ ላደረጉት ወልቂጤዎች በግራ መስመር ጥሩ ግልጋሎት የሰጠው አዳነ በላይነህ በሠራተኞቹ ቤት ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ጉዳይ ሲያነጋግር የቆየ ቢሆንም በመጨረሻም ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል አድሷል።

አዳነ በላይነህ ከዚህ ቀደም በወልቂጤ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ መድን እና አዲስ አበባ ከተማ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ወደ ወልቂጤ በመመለስ ተጫውቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!