ዩጋንዳዊው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ያስር ሙገርዋ ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ተስማማ፡፡
በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2009 ላይ የደቡብ አፍሪካው ኦርላንዶ ፓሬትስን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተቀላቅሎ ከቡድኑ ጋር የሊጉን ዋንጫ አግኝቷል። በመቀጠል በ2010 ወደ ፋሲል ከነማ አምርቶ የተጫወተ ሲሆን ከ2011 ግማሽ ዓመት አንስቶ ደግሞ ሊጉ በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ እስከተሰረዘበት ጊዜ ድረስ ለስሑል ሽረ እየተጫወተ ይገኝ ነበር። ተጫዋቹ ውሉ መጠናቀቁንም ተከትሎ ከስሑል ሽረ ጋር የተለያየ ሲሆን አንድ ዓመት ከግማሽ የቆየበትን ክለብ እና ደጋፊዎች አመስግኗል። በአንድ ዓመት የኮንትራት ዕድሜ የአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን ቡድንን ለመቀላቀልም ቅድመ ስምምነትን ፈፅሟል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ