በኮቪድ-19 ምክንያት የተራዘሙት የአፍሪካ ዋንጫ እና የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን ዛሬ ታውቋል።
ወደ 2022 የተሸጋገረው የ2021 የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚደረጉበትን ቀን ካፍ አሳውቋል። በዚህም መሠረት ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 8 ቀን 2013 ባሉት ቀናት የየምድቡ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በምድብ 11 የምትገኘው ኢትዮጵያም በተጠቀሱት ቀናት ከኒጀር ከሜዳዋ ውጪ እና በሜዳዋ በተከታታይ ትጫወታለች። የየምድቡ 5ኛ እና 6ኛ ጨዋታዎች ከመጋቢት 13- 21 ቀን 2013 ባሉት ቀናት ሲካሄድ ኢትዮጵያም ከማዳጋስካር በሜዳዋ እንዲሁም ከአይቮሪኮስት ከሜዳዋ ውጪ ታደርጋለች።
የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከግንቦት 23- ሰኔ 8 ባሉት ቀናት 1ኛ እና 2ኛ ጨዋታዎች እንዲሁም ከነሐሴ 24- መስከረም 7 ቀን 2014 የ3ኛ እና 4ኛ የምድብ ጨዋታዎች ይደረጋል። የየምድቡ 5ኛ እና 6ኛ ጨዋታዎች ደግሞ ከመስከረም 24- ጥቅምት 2 2014 ይደረጋል። ሌሶቶን በድምር ውጤት አሸንፋ ወደ ምድብ ድልድል በመግባት ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያም ወደፊት በሚወጣው መርሐ ግብር መሠረት ጨዋታዎች በተጠቀሱት ቀናት ታደርጋለች።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ