ሲዳማ ቡና የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

ሲዳማ ቡና የዮናታን ፍሰሀ እና ተስፉ ኤልያስን ውል ለማራዘም መስማማቱን ክለቡ እና ተጫዋቾቹ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታትን በሲዳማ ቡና የቀኝ መስመር ተከላካይ ቦታ ላይ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ዮናታን ፍሰሀ ውሉን ያራዘመ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ዘንድሮ ውሉ በሲዳማ መጠናቀቁን ተከትሎ በተለይ ከኢትዮጵያ ቡና በተደጋጋሚ ስሙ ሲነሳ የቆየ ሲሆን በመጨረሻ በክለቡ ለሁለት ዓመታት ለመቆየት ተስማምቷል፡፡

ሌላኛው ውሉን ያራዘመው ተስፉ ኤልያስ ነው፡፡ ከሀዋሳ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ድረስ ተጫውቶ ያሳለፈው ይህ የግራ መስመር ተሰላፊ ወላይታ ድቻን ከለቀቀ በኃላ ከ2011 ጀምሮ በሲዳማ ቡና ሲጫወት የቆየ ሲሆኑ ውሉን ለተጨማሪ ዓመት ያራዘመ አስራ ሦስተኛ ተጫዋች ሆኗል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!