አብርሃም መብራቱ ወይስ አዲስ አሰልጣኝ ?

‘የዓለም ዋንጫ እና የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች በጥቅምት ወር ይጀመራሉ’ ሲል ካፍ አስታውቋል። ዋልያዎቹስ ‘በእነዚህ ጨዋታዎች በማን ይመራሉ ?’ የሚለው ተጠባቂ ጉዳይ ሆኗል።

ሁለት ዓመታትን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ሲመሩ የነበሩት አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ሐምሌ 30 ውላቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ፌድሬሽኑ ‘ውድድሮች መቼ እንደሚደረጉ ስለማናውቅ ለብሔራዊ ቡድኑ ለጊዜው አሰልጣኝ አያስፈልገውም’ በሚል የአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱን እና የሌሎች አሰልጣኞችን ውል አለማራዘሙ ይታወሳል። በሌላ በኩል ካፍ ዛሬ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ መሠረት የዓለም እና የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች በቀጣዩ ዓመት ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ እንዲካሄዱ መወሰኑን በደብዳቤ መግለፁን በዘገባችን መጠቆማችን ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት ‘በጥቅምት ወር ዳግም ለሚጀምረው የማጣሪያ ጨዋታ ብሔራዊ ቡድናችን በቀድሞው አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ወይስ በአዲስ አሰልጣኝ ይቀርባል ?’ የሚለው ጥያቄ በቅርቡ ዕልባት እንደሚያገኝ ሰምተናል፡፡ በተለይ የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እንደገለፁልን ከሆነ ቴክኒክ ኮሚቴው ምክረ ሀሳብ ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከቀረበ በኋላ በምክረ ሀሳቡ መሠረት አዲስ ማስታወቂያ ይወጣል ወይስ ቴክኒክ ኮሚቴው ያቀረበው አሰልጣኝ በቀጥታ ይሾማል የሚሉት ጉዳዮች በቅርቡ መልስ እንድሚያገኙ ነግረውናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!