ፌዴሬሽኑ ከባየር ሙኒክ ጋር በመተባበር ለአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ ባየር ሙኒክ ጋር በመተባበር ዛሬ ማምሻውን በቪዲዮ አማካኝነት ለበርካታ የሀገራችን አሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ቶማስ ዶለር የቀድሞ የላዚዮ፣ ኤቨርተን እና አስቶቪላ ጀርመናዊ የአሁኑ የስፖርት ዳይሬክተር፣ አንቶኒዮ ሻታይ የቀድሞው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች፣ ክርስቶፎር ሎቺ የቀድሞው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች፣ ክላውስ ኦገንታለር እና ሀንስ ሀገን የተባሉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ናቸው ለአሰልጣኞቹ ስልጠናውን የሰጡት፡፡

ስልጠናው ያተኮረው በዋናነት አሰልጣኞች በቅድመ እና ድህረ የፕላን አወጣጥ እና አተገባበር ላይ ሲሆን ከውድድር በፊት የሚደረጉ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይም ሰፊ የሆነ ማብራሪያ ተሰጥቷል። ተሳታፊዎችም ሀሳብ እና ጥያቄ አቅርበው በቂ ምላሽ እንዳገኙ ሶከር ኢትዮጵያ ያገችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ከዚህ ቀደም ባየር ሙኒክ ስልጠና መስጠቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ የኮቪድ 19 ወቅት በመሆኑ በቪዲዮ አማካኝነት ሊሰጥ ችሏች። ወደፊት ወረርሺኙ ከተገታ በኋላ ወደ ሀገራችን መጥተው ስልጠና እንደሚሰጡም ሰምተናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!