ፈቱዲን ጀማል ወደ ቀድሞ ክለቡ ዳግም ለመመለስ ተስማማ

የመሐል ተከላካዩ ፈቱዲን ጀማል ከአንድ ዓመት የኢትዮጵያ ቡና ቆይታ በኃላ ዳግም የቀድሞው ክለቡን ለመቀላቀል ተስማማ፡፡

2010 መግቢያ ላይ ወላይታ ድቻን ከለቀቀ በኃላ በሲዳማ ቡና ሁለት ድንቅ ዓመታትን አሳልፏል፡፡ተጫዋቹ በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዘመን የአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን ስብስብም ተቀላቅሎ ከአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እስከ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ምርጥ አቋምን ሲያሳይ ከቆየ በኃላ ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቶ በድጋሚ የቀድሞው ክለቡ ሲዳማ ቡናን በሁለት ዓመት ውል ለመቀላቀል ዛሬ ረፋድ ተስማምቷል፡፡

ሲዳማ ቡና እስከ አሁን የአስራ ሶስት ነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት ያራዘመ ሲሆን ትላንት ያስር ሙገርዋን አዲስ ፈራሚ ለማድረግ ከተስማማ በኋላ በኃላ ሁለተኛው አዲስ የክለቡ ተጫዋች ፈቱዲን ጀማል ሆኗል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!