በዝውውር ገበያው እምብዛም እየተሳተፉ የማይገኙት የጦና ንቦቹ የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል ለማደስ ተስማምተዋል።
በአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች 4 ወጣት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል መስማማታቸው ይታወሳል። ከዚህ ጎን ለጎንም ቡድኑ የነባር ተጫዋቾችን ውል እያደሰ ይገኛል። ከደቂቃዎች በፊት ደግሞ ፈጣኑ አጥቂ ባዬ ገዛኸኝ ከቡድኑ ጋር ለቀጣይ 2 ዓመታት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።
ለስልጤ ወራቤ፣ ወላይታ ድቻ፣ መከላከያ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ጥሩ ግልጋሎት የሰጠው ይህ ተጫዋች በተሰረዘው የውድድር ዘመን ዳግም ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ ሲጫወት ታይቷል። ሊጉ እስከሚቋረጥ ድረስም 9 ግቦችን አስቆጥሮ 1 ግብ የሆነ ኳስ ለቡድን አጋሩ አመቻችቶ ማቀበሉ ይታወሳል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!