ሰበታ ከተማ የወሳኝ ተከላካዩን ውል አራዘመ

ተከላካዩ አንተነህ ተስፋዬ በሰበታ ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ተስማማ፡፡

የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ሲዳማን ከለቀቀ በኃላ በ2011 በድሬዳዋ ከተማ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን ዘንድሮ ሊጉ በኮሮና ቫይረስ እስከተሰረዘበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አዳጊው ሰበታ ከተማ አሳልፏል፡፡ ተጫዋቹ በብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ጉዳት ገጥሞት ክለቡን በተፈለገው ልክ ባያገለግልም በመጨረሻዎቹ የመቋረጫ ሳምንታት ግን ለክለቡ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎም ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ቢነሳም ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት በሰበታ ለመቆየት ተስማምቷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!