ሲዳማ ቡና አራተኛ ተጫዋቹን ለማስፈረም ተስማማ

ወጣቱ የአማካይ መስመር ተጫዋች የሆነው ተመስገን በጅሮንድ ለሲዳማ ቡና ለመፈረም ተስማማ፡፡

የቀድሞው የሺንሺቾ እና ደደቢት ተጫዋች በተሰረዘው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ክለብ ኢኮሥኮ ሲጫወት ከቆየ በኃላ በፕሪምየር ሊጉ ዳግም የሚመልሰውን የሁለት ዓመት ስምምነት ከሲዳማ ቡና ጋር ያረገው፡፡

በውል ማደስ ላይ ተጠምደው የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች ትናንት እና ዛሬ ተመስገንን ጨምሮ አራት ተጫዋቾች ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ተስማምተዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!