ድሬዳዋ ከተማ ተከላካይ ለማስፈረም ተስማምቷል

ድሬዳዋ ከተማ አራርሶ ጁንዲን ለሁለት ዓመት ለማስፈረም ተስማማ፡፡

የድሬዳዋ ከተማ ተወላጅ ተጫዋቾችን በይበልጥ ለቀጣዩ ዓመት ለመጠቀም ያሰቡ የሚመስሉት ብርቱካናማዎቹ የመሀል ተከላካዩ አራርሶ ጁንዲን በሁለት ዓመት ውል ለማስፈረም ነው የተስማሙት፡፡ ከድሬዳዋ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኃላ በከፍተኛ ሊጉ ናሽናል ሲሚንት ከዚህ ቀደም በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን 2010 ላይ ከኢትዮጵያ በመውጣት ለሶማሊያው ክለብ ሞቃዲሾ ለሁለት ዓመታት በመጫወት ካሳለፈ በኃላ ለድሬዳዋ የሁለት ዓመት ውል ለመፈረም ተስማምቷል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ