አጥቂው ገብረሚካኤል ያዕቆብ አዳማ ከተማን ለመቀላቀል ተስማማ፡፡
በአርባምንጭ ከተማ በፕሪምየር ሊጉ ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ ከቻለ በኃላ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ ከዚህ ቀደም መጫወት ሲችል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጠርቶ መጫወት ችሎ የነበረው ተጫዋቹ ሲዳማ ቡናን ከለቀቀ በኃላ በሀዋሳ ከተማም ተጫውቶ አሳልፏል፡፡ ወደ አርባምንጭ ከተማ ከተመለ በኋላ ቡድኑ በሊጉ በነበረበት ወቅት እንዲሁም በከፍተኛ ሊጉ ሲጫወት የቆየ ሲሆን በአንድ ዓመት የውል ኮንትራት አዳማ ከተማን ለመቀላቀል ቅድም ስምምነት በመፈፀም ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል፡፡ “በድጋሚ ወደ ፕሪምየር ሊጉ መመለሴ አስደስቶኛል ከዚህ ቀደም ለመጫወት እፈልገው ወደነበረው አዳማ መምጣቴም እጅግ ደስ ብሎኛል።” ሲል ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡
አዳማ ከተማዎች ገብረሚካኤል ያዕቆብን ጨምሮ እስከ አሁን ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ሲስማሙ ሦስት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ደግሞ ውል አድሰዋል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!