Soccer Ethiopia

አዳማ ከተማ ሦስት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማማ

Share

ከሰሞኑ ወደ ዝውውር እንቅስቃሴ የገባው አዳማ ከተማ ከከፍተኛ ሊጉ ሦስት ተጫዋቾች ለማስፈረም ተስማምቷል።

ከፈራሚዎቹ መሀል አንድነት አዳነ አንዱ ነው፡፡ ከአርባምንጭ ከተማ ታዳጊ ቡድን ተገኝቶ በክለቡ ያለፉትን አምስት ዓመታት በመሐል ተከላካይነት ያገለገለ ሲሆን ከአርባምንጭ ከተማ ጋር በፕሪምየር ሊጉም ሆነ በከፍተኛ ሊጉ ሲያገለግል ከቆየ በኃላ ወደ አዳማ ከተማ አምርቷል፡፡

ሌላኛው የአዳማ አዲሱ ፈራሚ አጥቂው ፍሰሀ ቶማስ ነው፡፡ ከመከላከያ ተስፋ ቡድን የተገኘው ይህ ወጣት ተጫዋች ዘንድሮ በከፍተኛ ሊጉ ሺንሺቶ ቆይታን ካደረገ በኃላ ለአዳማ ለመጫወት ተስማምቷል፡፡

ሦስተኛው የዛሬ ፈራሚ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ብርሀኑ አዳሙ ነው፡፡ ከአርባምንጭ ከተማ ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኃላ ለዋናውም ቡድን ተሰልፎ ያገለገለ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ ለሀምበሪቾ ከተማ በመጫወት አሳልፏል፡፡

አዳማዎች ከዛሬዎቹ ተጫዋቾች ቀደም ብለው አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ሲስማሙ የአምስት ነባር ተጫዋቾችን ውልም አድሰዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top