መረጃው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው።
ዓለም ዓቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ለኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ዳኛ ኢንስትራክተሮች ያዘጋጀው የ4ቀናት ስልጠና ዛሬ ነሐሴ 17/2012 ዓ.ም ተጀመረ።
በዚህ ስልጠና ላይየብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የኮሚቴው አባላትን ጨምሮ እና ኮርሱን አስተባባሪ ጨምሮ 37 ሙያተኞች ዛሬ በተጀመረው ስልጠና ላይ ተካፋይ ሆነዋል። ስልጠናው ላይ በመካፈል ላይ የሚገኙት ኢንስትራክተሮች ብዛት ደግሞ 27 ነው።
ይህ በzoom app በመታገዝ እየተሰጠ ያለው ስልጠና የ2020/21 ለውድድር ዘመን በተሻሻሉ የዳኝነት ህጎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ እና የኢንስትራክተሮች ሚና ምን መምሰል እንዳለበት እና የጨዋታ አሰሰሮች የሚሞሏቸው መረጃዎች ምን ሊሆኑ እንደሚገባ የተገለጸበት ነው።
ስልጠናውን ከደቡብ አፍሪካ ፌሊክስ ታጋዋሪማ እንዲሁም መንሱር ከፊፋ የአፍሪካ ሀገራት የዳኞች ተወካይ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን ለቀጣይ 3 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 7:30 ጀምሮ ለግማሽ ለግማሽ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።
ስልጠናው ለሀገራችን ኢንስትራክተሮች ትልቅ አቅምን የሚሰጥ እና በተሻሻሉ ህጎች ላይ የጋራ ግንዛቤን የሚይዙበት እንደሆነ የኢእፌ የስራ አስፈጻሚ አባል እና የዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኢብራሂም መሀመድ ለኢፉፌ ዌብሳይት ገልጸዋል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ