አዳማ ከተማዎች ግብጠባቂ ለማስፈረም ተስማሙ

አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም የሚገኙት አዳማ ከተማዎች ግብ ጠባቂው ታሪክ ጌትነትን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ቀደም ብለው ሌላው ግብ ጠባቂ ቶማስ ወዳጆን በማስማማት የዳንኤል ተሾመን ውል ያራዘሙት አዳማዎች ላለፉት ዓመታት የቡድኑነ ግብ ከጠበቀው ጃኮ ጋር እንደሚለያዩ የሚጠበቅ ከመሆኑ አንፃር ተጨማሪ ግብ ጠባቂ ሲፈልጉ ቆይተው ታሪክ ጌትነትን ለማስፈረም ማስማማት ችለዋል።

በተለያዩ ጊዜያት ከብሄራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶት የሀገሩን ማልያ ለብሶ የተጫወተው የቀድሞው የደደቢት እና ወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ ዐምና በዚት ወቅት ወደ አዳማ ለማምራት በቃል ደረጃ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ፊርማውን ለሀዲያ ሆሳዕና ፈርሞ በተሰረዘው የውድድር ዓመት ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ